You are currently viewing ለቤዛ የስነ-ዐዕምሮ ልዩ ክሊኒክ

ለቤዛ የስነ-ዐዕምሮ ልዩ ክሊኒክ

ድርጅታችን ጥራት ያለው የአዕምሮ ጤና አገልግሎትን ለማህበረሰባችን ተደራሽ ለማድረግ ስለ አዕምሮ ጤና ግንዛቤ ከማስጨበጥ ጀምሮ በጊዜ የመለየትና የተሻለ ህክምና ለመስጠት አላማ ይዞ በመስራት ላይ ይገኛል።
በዚሁ ረገድ ድርጅታችን ላለፉት 2 ኣመታት ከተለያዪ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጪ ከሚገኙ ድርጅቶች ጋር በትብብር አየሰራ ይገኛል ከነዚህም ውስጥ የአሜሪካን ኤምባሲ/ US Embassy፣ MSF,JHpiego,ARRA, International organization for migration, የኢትዮጽያ ንግድ ባንክአቢሲንያ ባንክብሄራዊ ባንክ ከብዙ በጥቂቱ የሚጠቅሱት ናቸው።
ለቤዛ የስነ-ዐዕምሮ ልዩ ክሊኒክ በመሃል አዲስ አበባ ከ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስትያን ወደ ካፒታል ሆቴል በሚወስደው መንገድ ላይ ከፕላዛ ሆቴል ጀርባ ፍጹም ሰላማዊና ምቹ በሆነ ቦታ ላይ የሚገኝ ሲሆን የተመላላሽ የአዕምሮ ህክምና፣የድንገተኛ የአዕምሮ ህክምና፣ የሱስ ህክምናን ጨምሮ ሌሎች የአዕምሮ ጤና አገልግሎቶችን ይሰጣል።

 

አገልግሎቶቻችን
ክሊኒካል አገልግሎት
1. የተኝቶ ህክምና አገልግሎት
1, ለድንገተኛ የአዕምሮ ህክምና ይህ አገልግሎት በሌሎች ሰዎችና በራሳቸው ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ብሎም ራሳቸውን ለማጥፋት የሚያስቡና የሚሞክሩ ታካሚዎች የሚቆዪበት ነው።
2, በመድሀኒት የታገዘ ልዩ የሱስ ህክምና ከዘመናዊ መድሃኒቶች ጋር ብሎም ሰላማዊና ምቹ ማገገምያ እንዲሁም ደህንነቱ የተጠበቀ ግቢ።
2. የተመላላሽ የአእምሮ ህክምና አገልግሎት
1, ለከባድ የአዕምሮ ህመም፣ለድብርት፣ለጭንቅትና ለፍርሃት፣
2, የአምቡላንስ አገልግሎት እና ድንገተኛ የአዕምሮ ህመም
3, የቡድንና የተናጥል የምክር ህክምና
4, ለጥንዶችና ለባለትዳሮች የምክር ህክምና
5, ለህጻናትና አረጋውያን፣እንዲሁም ለአዙሪት/ለሚጥል በሽታ
6, ለወሲብ ችግር እና ለእንቅልፍ መዛባት
7, ለተለያየ አላማ (ለጉዞ፣ለስራ) የሚውል አጠቃላይ የአዕምሮ ጤና ምዘና ለተልያዩ ተቋማት ማዘጋጀት
3. የተለያዩ ስልጠናዎች እና የማማከር አገልግሎች
1, ከስራ ጫና ጋር ተያይዘው ለሚመጡ ጭንቀት አና መፍትሄዎቻው
2, የተግባቦት መንገድና ዘዴዎች
3, የችግር ኣፈታትና ዘዴዎች
4, የስራ ጫና አና መሰላቸት መፍትሄዎች
5, የስነ-ልቦና የመጀመሪያ እርዳታ

4. የኢንተርኔት እና የቀጥታ የስልክ መስመር የህክምና አገልግሎት
ይህ አገልግሎት ታካሚዎች ካሉበት ቦታ ሆነው ክትትላቸው ሳይቆርጥ የ skype, what’s up, imo መተግበሪያዎችን በመጠቀም እንዲሁም የቀጥታ ስልክ መስመር በመጠቀም ሀኪማቸውን እንዲያገኙ ያስላቸዎል፡፡

ለበለጠ መረጃ

ስለ እኛ ለማወቅ

Lebeza.png

Leave a Reply